የዳግም ውልደት እውነታዎች
➙“እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።” (ዮሐ 3፥3)
መፅሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ዳግም ውልደት አያስተምርም። በተለምዶ የሰማነው ጌታን ስንቀበል የሰው መንፈስ ዳግመኛ እንደሚወለድ ነው። ነገር ግን አዲስ መንፈስ የሚወለደው የመጀመሪያው መንፈስ የት ሄዶ ነው? እውነታው ይህ ነው መንፈስ ኢመዋቲ (የማይሞት) ነው። መንፈስ አይበላሽም፣ አይረክስም እንዲሁም ዳግምም አይወለድም። አንዴ ይወለዳል ለዘለዓለም ከፍታውን ጠብቆ ይኖራል።
ሁሉም ሰው በምድር ከእናቱ ማህፀን ከመወለዱ በፊት ከእግዚአብሔር መንፈሱ ተወልዷል። መንፈስ ሰው ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም ነበር ሰው ከምድር በስጋ ሞቶ ሲለይም ይኖራል። በመሆኑም መንፈስ ስለማይጠፋ እና ስለማይመት የመንፈስ ዳግም መወለድ የሚባል ነገር የለም።
ዳግመኛ የሚወለደው የሰው ነፍስ ነው። በነፍስህ ዳግመኛ የምትወለደው መንግስተ ሰማይ ለመግባትአይደለም። ነገር ግን ከዚህ አለም ክፋት አምልጠህ የእግዚአብሔርን ህይወት እዚሁ ምድር ላይ መኖር እንድትጀምር ነው።
ለመንፈስ ዳግም መወለድ ትምህር ጥቅም ላይ የሚውለው ዋና ሀሳብ ዮሐንስ ምዕራፍ 3 ነው።ነገር ግሉ ቃል ስለ ዳግም መወለድ አይናገርም።
በዮሐንስ 3:3 ላይ "ዳግመኛ ካልተወለደ " ተብሎ የተተረጎመው የአራማይክ ቃል "አኖቴን-ጌኖ" (ánōthen gennáō) የሚል ሲሆን ትክክለኛ ትርጉሙ "ከላይ ካልተወለደ" ማለት ነው። ኢየሱስ "ከላይ" ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔር መንግስት ሊያይ አይችልም እያለ ነው። ወይም የእግዚአብሔር መንግስት የሚያየው ቀድሞ ከላይ (እግዚአብሔር) የተወለደ ሰው ብቻ ነው እያለ ነው። ዮሐንስ 3 ስለ መንፈስ የመጀመሪያ ውልደት እንጂ ስለ ሁለተኛ ውልደት የሚያወራ ክፍል አይደለም።
በተመሳሳይ 1ኛ ጴጥሮስ 1፥3 እና 23 ላይ ዳግም ውልደት የሚለው የግሪክ ቃል "አና-ጌኖ" (ana-gennáō) የሚለውን ቃል የሚጠቀም ሲሆን ይህ ቃል አኖቴን የሚለውን የአራማይክ ቃል "አና" ብሎ ይገልፀዋል። የሁለቱም ትርጉም "ከላይ" ማለት ነው። "አናጌኖ" የሚለው የግሪክ ቃል "አኖቴን ጌኖ" ከሚለው የአራማይክ ቃል ጋር ተመሳሳይ ፍቺ አለው።
በነገራችን ላይ በጊዜው ግሪክ መደበኛ የትምህርት ቋንቋ ሲሆን አራማይክ ከግሪክ ቋንቋ በአይሁድ ህዝብ የተወለደ ኢመደበኛ የመግባቢያ ቋንቋ ነው። አብዛኛውን ጊዜ የሚለያዩት በድምፅ ነው። ምን እያልኩ ነው የ1ኛ ጴጥሮስ 1፥3 እና 23 ሀሳብ ከዮሐንስ 3:3 ጋር ተመሳሳይ ነው። ክፍሎቹን ዳግም መወለድ ብለን ሳይሆን ከላይ መወለድ ብለን ልንረዳቸው ያስፈልጋል።
➙ዳግም መወለድ የሚለው የግሪክ ቃል "palingenesis" የሚል ሲሆን መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው በቲቶ 3:5 ላይ እና ማቲ 19:28 ላይ ብቻ ነው። እነዚህ ቃሎች ስለ ነፍስ ዳግም መወለድ እንጂ ስለ መንፈስ ዳግመኛ ልደት አይናገሩም።
➙“እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት (palingenesía) በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤” — ቲቶ 3፥5
በዚህ ጥቅስ ውስጥ አዲስ ልደት የሚለው ቃል በግሪኩ "ፓሊን ጄኔሲያ" (palin-genesía) ይላል። "ፓሊን" (palin) ማለት እንደገና ወይም ለሁለተኛ ጊዜ ማለት ነው። "ጄኔሲስ" (genesía) ማለት መፈጠር ወይም ህያው መሆን ማለት ነው። ዳግም ልደት የነፍሳችን ሙሉ በሙሉ መታደስን ወይም ከውድቀት ፊት ወደ ነበረው የአስተሳሰብ ከፍታ መመለስ ነው። ወይም ዳግም ልደት ማለት እንደገና ወደ ስማያዊ አስተሳሰብ መውጣት ነው። ቆላ3:1-3
➙“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው #አዲስ_ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ።” ማቴ 19፥28 (አ.መ.ት)
"አዲስ ልደት" የሚለው ቃል "ፓሊን ጄኔሲያ" የሚል ሲሆን የ1954 ትርጉም ቃሉን "በዳግመኛ ልደት" በማለት ተርጉሞታል።
ከሀይማኖት መንግስት ሰማይ ለመግባት "ዳግመኛ መወለድ" እንዳለብን ተምረናል። ጌታ ስትቀበል፣ የኃጢአተኞችን ፀሎት እጅህን አንስተህ ስትፀል፣ ከጌታ ጋር ዳግመኛ ክፉ ነገር ላለማድረግ ቃል ኪዳን ስትገባ ዳግመኛ እንደምንውለድ ተነግሮናል። ይህ ግን የተሳሳተ ነው።
ማንም በሚገባው ቃል ኪዳን ከክፉ ነገር መመለስ አይቻለውም። የሰውን ህይወት የሚለውጠው ነፍሳችን በቃሉ ወተት ሞታ (ታድሳ) ዳግም ስትወለድና ስታድግ ብቻ ነው። ነፍስን ዳግም መውለድ የሚችል መግነጢሳዊ ውሳኔ የለም። ማንም ሰው በአንድ ቀን ጥሩ ውሳኔ ዳግም ሊወለድ አይችልም። ለራሳችን በመወሰንም ራሳችንን ልንወልድ አንችልም። በመወሰን እግዚአብሔርን አባት እንዲሆነን ልናስገድደው አይችልም።
ነፍስ ዳግም የሚወለደው በመጥፍት ነው። ኢየሱስ ነፍሱን የሚያጠፍ ያገኛታል ብሏል። በአለማዊ ልማድና ትምህርት የሰበሰብነው ከእግዚአብሔር እውቀት ተቃራኒ የሆነ የነፍስ እውቀት ሁሉ በቃሉ መገለጥ ወተት ቀስበቀስ እየጠፍ ይሄዳል።
የቀደመው ነፍስ ሲሞት አዲስ ሰማያዊ ነፍስ ዳግመኛ ይወለዳል። የነፍስን ውልደት ዳግመኛ የምንለው መጀመሪያ የነበርንበት ነገር ግን በአዳም ምክንያት የጠፍንበት ስለሆነ ነው።

Comments
Post a Comment