እግዚአብሔር "በስሜ የተጠራው ህዝቤ" ሲል ምን እያለ ነው?
በመንፈሳዊ አለም ስርዓት ስም አንድን ግለሰብ ከሌላ ግለሰብ ለመለየት የሚሰጥ መጠሪያ ብቻ አይደለም። በእግዚአብሔር አለም ስም ማንነት ነው። ስም ማንነትህን የሚገልፅ አንድ ቃል ነው። ስም የማንነትህን ምንጭ የሚገልፅ ቃል ነው። ስም አቅምህን፣ አላማህንና ዘላለምህን የሚያብራራ ሀሳብ ነው።
እግዚአብሔር ሰውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈጥር የራሱን የተሟላ "መልክና አምሳል" በማካፈል ፈጥሮታል። ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል ማለት ሰው እግዚአብሔር ሊጠራበት ወይም ሊታወቅበት ከሚችለው ከማንኛውም ስም (ማንነት) በታይ አይደለም ማለት ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር የሚጠራበት ስም ሁሉ አዳምም የሚጠራበት ስም ነው። ሀሌሉያ!
ይሁን እንጂ አዳም በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ከተፈጠረው ከመንፈሱ ራሱን (ስሙን፣ ማንነቱን) ከመጥራት (ከማወቅና ከመመዘን) ይልቅ ከውጪ (በስጋ) ከሆነው፣ ካደረገውና ማድረግ ከሚፈልገው አንፃር መጥራት (መሰየም፣ መመዘን) ጀመረ። ይህ አዳም የወደቀበት ራስን (ስምን) በስጋ ከሰራው ስራ ተነስቶ የመጥራት (የመመዘን) የተሳሳተ አለማዊ ስርዓት ሰዎች ሁሉ ከአዳም የወረስነው ኃጢአት ነው። በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ስም (ማንነት) የተጠራው የሰው ዘር በማድረግና ባለማድረግ ስም (ማንነት) ላይ ወደቀ።
ለአንድ ህፃን ወላጆች ከሚያወጡለት የምኞት መጠሪያ ስም በተጨማሪ ከአለም የህግ ስርዓት በታች የሚኖር ማነኛውም ሰው ከህፃንነት እያደገ ሲመጣ ከአስተዳደግ ሁኔታዎች፣ ከሚያልፉበት ታሪክ፣ ከአከባቢ፣ ከሀይማኖት፣ ከዘር፣ ካለውና ከሌለው ነገር፣ ካደረገውና ካላደረገው ነገር እንዲሁም ከሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በመነሳት ስሙን (ራሱን፣ ማንነቱን) ለመሰየም ለመመዘን ለመጥራት ባሪያ ነው።
እግዚአብሔር ግን ከአብረሃም ጀምሮ የስሙን ወንጌል በማብሰር በእምነት አማካኝነት የሰው ልጆች በድጋሚ ራሳቸውን በእግዚአብሔር ስም እንዲጠሩ የማዳን ስራውን ጀመረ። መፅሐፍ ቅዱስ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ስም የተጠሩ ቅዱስ ህዝቦች እንደሆኑ ይነግረናል። (2 ዜና 7፥14፣ ኢሳ 43፥6-7)
በእግዚአብሔር ስም መጠራት ማለት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ባሪና ማንነት መታወቅ ማለት ነው። የእግዚአብሔር ማንነት የእስራኤላውያን መታወቂያ ሲሆን ማለት ነው። ይህ ለእስራኤላውያን መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠው የእግዚአብሔር ስም (ማንነት) አሁን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ለአህዛብ (ለሰው ዘር በሙሉ) መጠሪያ እንዲሆን ተዋጅቷል።
የመንፈስ ቅዱስ ማፅናናት
ፓራክሊቶስ "paráklētos" የሚለው የግሪክ ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ 5 ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። ከአምስቱ መካከል 4ቱ የሚገኘው በዮሐንስ ወንጌል ላይ ሲሆን አንዱ ደግሞ በዮሐንስ መልዕክት ውስጥ ነው።
ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል 14:16፣ 14:26፣ 15:26 እና 16:7 ላይ ከእርሱ በኃላ የሚመጣውን መንፈስ ቅዱስ "ፓራክሊቶስ" (paráklētos) ብሎ ገልፆታል። የአማረኛም ሆነ የእንግሊዝኛ መፅሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ይህንን የግሪክ ቃል አራቱም ቦታ ላይ "አፅናኝ" (comforter) ብለው ተርጉመውታል።
በመጀመሪ አፅናኝ የሚለው ትርጉም እንመልከት። ቃሉን አፅናኝ የሚል ትርጉም የተሰጠው በአንድምታው (implication) ነው። ፓራክሊቶስ "paráklētos" በቀጥታ ሲተረጎም ከሁለት ቃሎች የተገነባ ቃል ነው። የመጀመሪያው ፓራ (para) ሲሆን ትርጉሙ ከጎን መሆን ወይም አብሮ መሆን ማለት ነው። ሁለተኛው ቃል ክሌቶስ (kletos) ሲሆን ካሊኦ (kaleo) ከሚለው ስር ቃል የመጣ ቃል ነው። ትርጉሙ መጥራት ማለት ነው።
ስለዚህ የፓራክሊቶስ "paráklētos" ቀጥተኛ ትርጉም "አብሮ ሆኖ የሚጠራ" ወይም "ከጎናችን ሆኖ የሚጠራ" ማለት ነው። ያው የዚህ እንድምታ አፅናኝነትን የሚገልፅ በመሆኑ "አፅናኝ" የሚል የእንድምታ ትርጉም ተሰጥቶታል።
አሁን ጥያቄው መንፈስ ቅዱስ ምን ብሎ ነው የሚጠራን? ወይም ከየት ነው የሚጠራን የሚለው ነው። መጥራት (kaleo) የሚለው ቃል ሁለት አይነት ትርጉም አለው። የመጀመሪያ አንድ ሰው ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ መጥራት ሲሆን ሁለተኛው አንድን ሰው በመጠሪያ ስም መጥራት ወይም መሰየም ነው።
ከዮሐንስ ወንጌል 14 ጀምሮ ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ ህብረት የሚኖረን እኛ አማኞች ነን። አማኞች ማለት ወደ ክርስቶስ ህይወት የመጣን ማለት ነው። በመሆኑም ኢየሱስ አፅናኝ ወይም አብሮ ሆኖ የሚጠራ ሲል ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ሳይሆን በአንድ ልዩ ስም መጥራትን የሚያመለክት ሆኖ እናገኘዋለን።
ስለዚህ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ፓራክሊቶስ "paráklētos" ሲል በትክክለኛው ስማችሁ እለት እለት አብሮአችሁ መሆን የሚጠራችሁ እያለ ነው። የሰው ትክክለኛ ስያሜ ከእግዚአብሔር አባት ማንነት የሚነሳ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን የኤፌሶን 3:14-15 ላይ እንዲህ ይነግረናል። "በዚህም ምክንያት #በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ ከእርሱም በሰማይና በምድር ያለ ቤተሰብ ሁሉ #ስያሜ ያገኛል።"
መንፈስ ቅዱስ የሚጠራን ከሁኔታዎች በምናገኘው ተቀያያሪ ስም ሳይሆን ከእግዚአብሔር ባገኘነው በክርስቶስ ባለን ማንነት ነው። የመንፈስ ቅዱስን ለዘላለም አብሮን መሆን ዋጋ የሚሰጠው ይሄ ነው። ያለንበት ምድራዊ ሁኔታ ራሳችንን ከሁኔታዎች ተነስተን እንድንመዝንና እንድንሰይም ሲታገለን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሆኖ ከእግዚአብሔር በተካፈልነው መልክና አምሳል (በእውነተኛው ማንነት) ይጠራናል። ሁኔታው ባሪያ፣ ደካማዎች ፣ ኃጢአተኛ፣ የማይጠቅም፣ ተራ፣ የተጠላ፣ ከንቱ ብሎ ሲጠራን መንፈስ ቅዱስ ከጎናችን ሆኑ ይህ የሁኔታው ድምፅ ውሸት ነው አንተ ልጅ ነህ፣ፃድቅ ነህ፣ ብርቱ ነህ፣ ክቡር ነህ፣ የምትጠቅም ነህ የተወደድክ ነህ ይላል። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ስራ ፓራክሊቶስ የሚል ልዩ ስም እንዲሰጠው አድርጎታል።
አሁን ጥያቄው ይህ "ፓራክሊቶስ" የሚለው ቃል በ1ዮሐንስ መልዕክት 2:1 ላይ "ጠበቃ" የሚል ትርጉም ለምን ተሰጠው የሚለው ነው። ቃሉ እንዲህ ይላል። "ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ (paráklētos) አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ "ፓራክሊቶስ" (paráklētos) ብሎ የጠራው መንፈስ ቅዱስን ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው።
ይህ ቃል በአብዛኛው ኢየሱስ አማላጅ ነው ለማለት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። ይህ ማለት እኛ ኃጢአት ስንሰራ እግዚአብሔር ድራሻችንን ሊያጠፍን ሲነሳ ኢየሱስ ደግሞ የእኛ ጠበቃ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ይከራከርና አሸንፎ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንተርፍለን ማለት ነው። ይህ የተሳሳተ ትምህርት ነው።
ከላይ በተመለከትነው "ፓራክሊቶስ" (paráklētos) መሰረት ይህ ቃል ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ እኛ እንደሚከራከር አይናገርም። እግዚአብሔር ኢየሱስ ዳኛና ጠበቃ ሆነው አያውቁም። ሐዋሪያው መልዕክቴን የፃፍኩላችሁ ኃጢያት እንዳትሰሩ (ስለ ራሳችሁ የተሳሳተ ማንነትን እንዳታምኑ) ነው፤ ነገር ግን እኔ እንዲህ ነኝ ብላችሁ ስለ ራሳችሁ ውሸት የሆነውን ብታምኑም እንኳን በእግዚአብሔር ፊት ግን የእናንተ ትክክለኛ ስም ሆኖ የሚጠራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እናንተ ስለ ራሳችሁ የምታምኑት ማነኛውም የውሸት ማንነት በዙፍን ክፍል ውስጥ ተቀባይነት የለውም እያለ ነው።

Comments
Post a Comment