ማንን ትመስላለህ
“በዚህ ገንዘብ ላይ የሚታየው መልክ የማን ነው?” ማቴ 22፥20
እስኪ ልብ ብላችሁ ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱ ማንን ትመስላላችሁ? መልካችሁ የማንን ይመስላል? ለምን ራሳችሁን ብቻ አሁን ከጎናችሁ ያለውን ሰው ተመልከቱት? የእግዚአብሔር መልክ አይታያችሁም? ፍቅር፣ የዋህነት፣ ነፃነት፣ እረፍት አይታያችሁም?
በእርግጥ ስንሰራ ከጅምሩ የተሰራነው በእግዚአብሔር ንድፍ (model) ነው። የሰራን የራሱን መልክና አምሳል እየተመለከተ ነው። የሰራን እንደ ራሱ ግሩምና ድንቅ አድርጎ ነው። (ዘፍ1:26/መዝ139:14)
ኢየሱስ “የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” ያለው ምን እያሰበ ነው? (ማቴ 22፥21) መንግስትን ስለሚያሳስበው ግብር ወይም ሃይማኖትን ስለሚያሳስበው አስራት የመክፈል ትምህርት እያስተማረ ነው? በፍፁም አይደለም። ግብርም ሆነ አስራትን መስጠት መንፈሳዊ ትምህርት የሚያስፈልገው ሚስጥር አይደለም።
ኢየሱስ በሰው ላይ የተሳለው የእግዚአብሔር መልክ ነው እያለ ነው። የመጣሁት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ልዋጅ/ ልሰጥ ነው እያለ ነው። እግዚአብሔር ራሱ በአንተ ላይ የቀረፅኩት የራሴን መልክ ነውና አንተ የእኔ ነህ እያለ ነው።
መፅሐፍ “የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ አምላክ በሰው ሙያና ጥበብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ ይመስላል ብለን ማሰብ አይገባንም።” በማለት ይነግረናል። (ሐዋ 17፥29) አምላክ የሚመስለው ሰውን ነው። ሰውም የሚመስለው አምላክን ነው። ዝምድናችን የሩቅ ሳይሆን የአባትና የልጅ ነው። ችርስ!
ስለዚህ የእግዚአብሔር መልክ ስላለብህ የእግዚአብሔር ነህ። ልጅ ከሆንክ የአባትህ ነህ። የአባትህ መልክ በአንተ ላይ ስለተሳለ አንተ የእግዚአብሔር ነህ። እኔም የእግዚአብሔር ነኝ። ሁላችንም የጌታ ነን። ሁላችንም በክርስቶስ ለእግዚአብሔር ተዋጅተናል። አሜን! እንዴት ደስ ይላል።

ብዙዎች እንደሚያስቡት እግዚአብሔር አዛዥ ወይም ማዘዝ የሚወድ አምላክ አይደለም ነገር ግን የእውነት አምላክ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ ስለ ፍጥረት አጀማመር ሲያሳየው ሰው እንዴት እንደ ተፈጠረ አሳየው እንጂ ሰው እንዴት መኖር እንዳለበት ትዕዛዝን አልሰጠውም።
ሙሴም ከሰው ጋር ተያይዞ ያየውን ራዕይ እንዲህ በማለት በአጽዕኖት አስቀምጦታል። ‘እግዚአብሔርም “ሰውን በመልካችንና በአምሳላችን እንስራ…“ አለ ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው’ (ዘፍ 1፥26-27) 🤗👋🤩
Don't try to be, Just know and believe who you are. then you will be without a single try!
Comments
Post a Comment