ችግሩ አስተሳሰባችን ነው።
የኢየሱስና የሐዋርያቱ ዋና መልዕክት "ንስሀ ግቡ" የሚል ነው። ንስሐ በግሪክ "ሜታኖያ" (metanoia) ማለት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ በእውቀት መታደስ ወይም የእውቀት አንድነት መፍጠር ማለት ነው። ንስሐ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ወደ አንድ አስተሳሰብ መምጣት ማለት ነው።
የሰው ልጆች መፍትሔ የሚያስፈልገው ምንም አይነት ተፈጥሮአዊ ችግር የለብንም። ኢየሱስ ተፈጥሮአችንን ሊለውጥ አልመጣም። ማንነታችን ምንም አይነት አደጋ በማያገኘው በእግዚአብሔር መልክና ምሳል ንድፍ የተሰራ ነው። (ዘፍ1:27)
ታዲያ መፍትሔ ያስፈለገው የሰው ልጆች ችግር ምንድነው? በመጀመሪያው አዳም ምክንያት የተከሰተው ምንድነው? የወደቅነው የቱጋ ነው? የወደቅነው በአስተሳሰባችን ነው። ችግራችን ኃጢአት ነው። ኃጢአት የተሳሳተ አመለካከት ነው። ችግራችን በሙሉ ማንነታችን ላይ ሳይሆን ስለ ማንነታችን ያለን የተሳሳተ አመለካከት ነው።
➙ችግራችን መልክና አምሳልን ሳይሆን ራቁትነትን ማወቅ ነው👉 "የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ ዕራቍታቸውን መሆናቸውንም #ተገነዘቡ። ስለዚህ የበለስ ቅጠል ሰፍተው አገለደሙ።" ዘፍ 3:7
➙ችግራችን ምንጫችንን መርሳት ነው👉 "አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤ የወለደህን አምላክ #ረሳኸው።" ዘዳ 32:18
➙ችግራችን የተሳሳተ እይታ ነው👉 " ራሳችንን #ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።” ዘኍ 13:33
➙ችግራችን ስለማንነታችን እውነት የሆነውን አለማመን ነው👉“እነርሱ #ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ" ሮሜ 11፥20
➙ችግራችን አስተሳሰባችን ላይ ነው👉 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ ... ሐሳቤም #ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።" ኢሳ 55:9
➙ችግራችን ልቦናችን ላይ ነው👉 "ነገር ግን ብሉይ ኪዳን በተነበበ ቍጥር፣ ያ መሸፈኛ እስከ ዛሬ ድረስ ስላልተወገደ #ልቡናቸው እንደ ደነዘዘ ነው" 2 ቆሮ 3:14 /
➙ችግራችን ማን እንደሆንን አለማወቅ ነው👉“እነርሱ #ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤” ኤፌ 4፥18
➙ችግራችን የአስተሳባችን ከንቱነት ነው👉 "#በአስተሳሰባቸው ከንቱነት እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ልትመላለሱ አይገባም። ኤፌ 4:17
➙ችግራችን አይናችን ላይ ነው👉 “#ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል" ማቴ 6፥23/ራዕ 3:18
አዎ ችግራችን መንፈሳችን ላይ ሳይሆን ነፍሳችን (የእውቀት ክፍል) ላይ ነው። ሁለተኛ አዳም (ክርስቶስ) ከመጀመሪያ አዳም ስለ ማንነታችን የወረስነውን የውሸት እውቀት ሁሉ ለመደምሰስ "የነፍሳችን ቤዛ" ..."የነፍሳችን መልህቅ"... "የነፍሳችን አዳኝ" ሆኖ የተገለጠው ለዚህ ነው። ሀሌሉያ አደረገው!
Comments
Post a Comment