Posts

የዳግም ውልደት እውነታዎች

 ➙“እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።” (ዮሐ 3፥3) መፅሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ዳግም ውልደት አያስተምርም። በተለምዶ የሰማነው ጌታን ስንቀበል የሰው መንፈስ ዳግመኛ እንደሚወለድ ነው። ነገር ግን  አዲስ መንፈስ የሚወለደው የመጀመሪያው መንፈስ የት ሄዶ ነው? እውነታው ይህ ነው መንፈስ ኢመዋቲ (የማይሞት) ነው። መንፈስ አይበላሽም፣ አይረክስም እንዲሁም ዳግምም አይወለድም። አንዴ ይወለዳል ለዘለዓለም ከፍታውን ጠብቆ ይኖራል። ሁሉም ሰው በምድር ከእናቱ ማህፀን ከመወለዱ በፊት ከእግዚአብሔር መንፈሱ ተወልዷል። መንፈስ ሰው ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም ነበር ሰው ከምድር በስጋ ሞቶ ሲለይም ይኖራል። በመሆኑም መንፈስ ስለማይጠፋ እና ስለማይመት የመንፈስ ዳግም መወለድ የሚባል ነገር የለም። ዳግመኛ የሚወለደው የሰው ነፍስ ነው። በነፍስህ ዳግመኛ የምትወለደው መንግስተ ሰማይ ለመግባትአይደለም። ነገር ግን ከዚህ አለም ክፋት አምልጠህ የእግዚአብሔርን ህይወት እዚሁ ምድር ላይ መኖር እንድትጀምር ነው። ለመንፈስ ዳግም መወለድ ትምህር ጥቅም ላይ የሚውለው ዋና ሀሳብ ዮሐንስ ምዕራፍ 3 ነው።ነገር ግሉ ቃል ስለ ዳግም መወለድ አይናገርም። በዮሐንስ 3:3 ላይ "ዳግመኛ ካልተወለደ " ተብሎ የተተረጎመው የአራማይክ ቃል "አኖቴን-ጌኖ"  (ánōthen gennáō) የሚል ሲሆን ትክክለኛ ትርጉሙ "ከላይ ካልተወለደ" ማለት ነው። ኢየሱስ "ከላይ" ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔር መንግስት ሊያይ አይችልም እያለ ነው። ወይም የእግዚአብሔር መንግስት የሚያየው ቀድሞ ከላይ (እግዚአብሔር) የተወለደ ሰው ብቻ ነው እያለ ነው። ዮሐንስ 3 ስለ መንፈስ የመጀመሪያ ው...

እግዚአብሔር "በስሜ የተጠራው ህዝቤ" ሲል ምን እያለ ነው?

Image
በመንፈሳዊ አለም ስርዓት ስም አንድን ግለሰብ ከሌላ ግለሰብ ለመለየት የሚሰጥ መጠሪያ ብቻ አይደለም። በእግዚአብሔር አለም ስም ማንነት ነው። ስም ማንነትህን የሚገልፅ አንድ ቃል ነው። ስም የማንነትህን ምንጭ የሚገልፅ ቃል ነው። ስም አቅምህን፣ አላማህንና ዘላለምህን የሚያብራራ ሀሳብ ነው። እግዚአብሔር ሰውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈጥር የራሱን የተሟላ "መልክና አምሳል" በማካፈል ፈጥሮታል። ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል ማለት ሰው እግዚአብሔር ሊጠራበት ወይም ሊታወቅበት ከሚችለው ከማንኛውም ስም (ማንነት) በታይ አይደለም ማለት ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር የሚጠራበት ስም ሁሉ አዳምም የሚጠራበት ስም ነው። ሀሌሉያ! ይሁን እንጂ አዳም በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ከተፈጠረው ከመንፈሱ ራሱን (ስሙን፣ ማንነቱን)  ከመጥራት (ከማወቅና ከመመዘን) ይልቅ ከውጪ (በስጋ) ከሆነው፣ ካደረገውና ማድረግ ከሚፈልገው አንፃር መጥራት (መሰየም፣ መመዘን) ጀመረ። ይህ አዳም የወደቀበት ራስን (ስምን) በስጋ ከሰራው ስራ ተነስቶ የመጥራት (የመመዘን) የተሳሳተ አለማዊ ስርዓት ሰዎች ሁሉ ከአዳም የወረስነው ኃጢአት ነው። በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ስም (ማንነት) የተጠራው የሰው ዘር በማድረግና ባለማድረግ ስም (ማንነት) ላይ ወደቀ። ለአንድ ህፃን ወላጆች ከሚያወጡለት የምኞት መጠሪያ ስም በተጨማሪ ከአለም የህግ ስርዓት በታች የሚኖር ማነኛውም ሰው ከህፃንነት እያደገ ሲመጣ ከአስተዳደግ ሁኔታዎች፣ ከሚያልፉበት ታሪክ፣ ከአከባቢ፣ ከሀይማኖት፣ ከዘር፣ ካለውና ከሌለው ነገር፣ ካደረገውና ካላደረገው ነገር እንዲሁም ከሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በመነሳት ስሙን (ራሱን፣ ማንነቱን)  ለመሰየም ለመመዘን ለመጥራት ባሪያ ነው። እግዚአብሔር ግን ከአብረ...

ማንን ትመስላለህ

“በዚህ ገንዘብ ላይ የሚታየው መልክ የማን ነው?”  ማቴ 22፥20  እስኪ ልብ ብላችሁ ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱ ማንን ትመስላላችሁ? መልካችሁ የማንን ይመስላል? ለምን ራሳችሁን ብቻ አሁን ከጎናችሁ ያለውን ሰው ተመልከቱት?  የእግዚአብሔር መልክ አይታያችሁም? ፍቅር፣ የዋህነት፣ ነፃነት፣ እረፍት  አይታያችሁም? በእርግጥ ስንሰራ ከጅምሩ የተሰራነው በእግዚአብሔር ንድፍ (model) ነው። የሰራን የራሱን መልክና አምሳል እየተመለከተ ነው። የሰራን እንደ ራሱ ግሩምና ድንቅ አድርጎ ነው። (ዘፍ1:26/መዝ139:14) ኢየሱስ “የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” ያለው ምን እያሰበ ነው? (ማቴ 22፥21) መንግስትን ስለሚያሳስበው ግብር ወይም ሃይማኖትን ስለሚያሳስበው አስራት የመክፈል ትምህርት እያስተማረ ነው? በፍፁም አይደለም። ግብርም ሆነ አስራትን መስጠት መንፈሳዊ ትምህርት የሚያስፈልገው ሚስጥር አይደለም። ኢየሱስ በሰው ላይ የተሳለው የእግዚአብሔር መልክ ነው እያለ ነው። የመጣሁት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ልዋጅ/ ልሰጥ ነው እያለ ነው። እግዚአብሔር ራሱ በአንተ ላይ የቀረፅኩት የራሴን መልክ ነውና አንተ የእኔ ነህ እያለ ነው። መፅሐፍ “የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ አምላክ በሰው ሙያና ጥበብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ ይመስላል ብለን ማሰብ አይገባንም።” በማለት ይነግረናል። (ሐዋ 17፥29) አምላክ የሚመስለው ሰውን ነው። ሰውም የሚመስለው አምላክን ነው። ዝምድናችን የሩቅ ሳይሆን የአባትና የልጅ ነው። ችርስ! ስለዚህ የእግዚአብሔር መልክ ስላለብህ የእግዚአብሔር ነህ። ልጅ ከሆንክ የአባትህ ነህ። የአባትህ መልክ በአንተ ላይ ስለተሳለ አንተ የእግዚአብሔር ነህ። እኔም የእግዚአብሔር ነኝ። ሁ...