በኃጢያት ምክንያት እግዚአብሔር ተለይቶናል?
በፍፁም! እግዚአብሔር ከሰው ጋር ተለያይቶ አያውቅም። ከሰው ተደብቆ አያውቅም። መለያየት በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የተፈጠረ የተሳሳተ አመለካከት ነው። የመለያየት ትምህርት ከምናልፍበት ጊዜያዊ ስሜት የተፈበረከ የውሸት እውቀት ነው። አዳም ኃጢአትን ወደ አዕምሮ አስገብቶ ሲያምን (ፍሬውን ሲበላ) ከእግዚአብሔር ሸሸ እንጂ እግዚአብሔር ከአዳም አልሸሸም።(ዘፍ3:8) እግዚአብሔር መልካም ሰርተህልኛል ብሎ ያልቀረበውን ሰው ክፉ አድርገሀል ብሎ አይለየውም። አዳም ተደበቀ እንጂ እግዚአብሔር አልተደበቀም። አዳም ራቁቴን ነኝ አለ እንጂ እግዚአብሔር ራቁትህን ነህ አላለውም። (ዘፍ3:7) እንዲያውም “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ?" የእግዚአብሔር ጥያቄ ነበር።(ዘፍ3:11) ራቁትነት በእግዚአብሔር የተረጋገጠ እውነት ሳይሆን በሰው የታመነ #የውሸት_እውቀት ነው። ራቁትነት ከእባቡ (ዲያቢሎስ) ስለ ማንነታችን የተነገረን የውሸት እውቀት ነው። ኃጢያት ማለት አምነን የተቀበልነው ራቁቴን ነኝ የሚል የውሸት እውቀት ነው። ኃጢአት በሰው ውስጥ ኮነኔን ይፈጥራል። ነገር ግን እኛ ስለተኮነንን እግዚአብሔር አፍሮብናል ማለት አይደለም። እኛ ስለ ማንነታችን ውሸትን አምነናል ማለት እግዚአብሔርም ስለ እኛ ውሸት ያምናል ማለት አይደለም። እግዚአብሔር ከአዳም ውድቀት በፊትም ሆነ በኃላ ስለ አዳም ያለው አመለካከት የፀና ነው። አዳም በመልኩና በአምሳሉ የወለደው ልጁ ነው። (ዘፍ1:27፣ሉቃ3:38) ልጅ ጭቃ ነካ ተብሎ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ አይጨመርም። ወርቅ ስለ ቆሸሸ ክብሩን አያጣም። አብርሀም አጋር ቤት ስለ ገባ ታላቅ ዋጋው ዝቅ አይልም።(ዘፍ15:1) ከ100 በጎች መሀከል አንዱ ተለይቶ የጠፍ በግ እንጂ ወደ ተኩላነት አይቀየርም።(ሉቃ15:6) ንስር ከዶሮ ጋር ...